የኢራን ሕዝብ በቦምብ እየተደበደበ ባለበት ወቅት ስለ ነዳጅ ዋጋ መደራደር ተቀባይነት የለውም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
16:52 30.03.2026 (የተሻሻለ: 16:54 30.03.2026)
ሰብስክራይብ
የኢራን ሕዝብ በቦምብ እየተደበደበ ባለበት ወቅት ስለ ነዳጅ ዋጋ መደራደር ተቀባይነት የለውም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እስማኤል ባጋይ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
በቅርብ ግዜያት ከአሜሪካውያን ጋር ምንም ዓይነት ድርድር አልተደረገም።
"ዴና" በተሰኘችው መርከብ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ የኢራን መርከበኞችን የመፈለግ ሥራ እንኳን አልተፈቀደም።
አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ተቋማት ላይ ለፈጸሙት ድርጊት ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምንም ዓይነት ምላሽ አልተሰጠም።
የኤጀንሲው ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ አጥቂዎቹን ከመኮነን ይልቅ ሁኔታውን ይበልጥ የሚያወሳስቡ አገላለጾችን ተጠቅመዋል።
የኢራን አምባሳደር በቤይሩት ሥራቸውን ቀጥለዋል።
በሆርሙዝ ሰርጥ ዙሪያ ኢራን የወሰደቻቸው እርምጃዎች የሚያልፉ መርከቦች የጠላት አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ ያለሙ ናቸው።
የቀጣናው ሀገራት ሀገራቸውን ወደ አውዳሚ ጦርነት የመሩት ዘለንስኪ "እንዲበዘብዟቸው" የማይፈቅዱ "ብልህ" ሀገሮች ናቸው።
በዩክሬን ያለውን ግጭት እስራኤል እና አሜሪካ ኢራን ላይ ከፈጸሙት ግልጽ ጠብ አጫሪ ጥቃት ጋር ማገናኘት ከባድ የሆነ ስሁት ስሌት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X