ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ የባሕል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ፌስቲቫልን እንድታዘጋጅ ተመረጠች

ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.03.2026
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የአፍሪካ የባሕል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ፌስቲቫልን እንድታዘጋጅ ተመረጠች

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የ2026 አኅጉራዊ ውድድር መላው አፍሪካውያን ልዩ ባሕላዊ ጨዋታዎቻቸውን ይዘው የሚቀርቡበት፣ የአኅጉሪቱ ወጣቶች የሚገናኙበት እና የባሕል ልውውጥ የሚያደርጉበት ደማቅ መድረክ ይሆናል ተብሏል።

የመጀመሪያው የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች ፌስቲቫል በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መወሰኑ ለሀገራዊ ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ሲሉ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ መኪዩ መሀመድ ተናግረዋል፡፡


የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን ሊቀመንበር ዶ/ር ኪይካማቱዋ፤ "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ባሕል እና ታሪክ መገኛ በመሆኗ ይህንን ውድድር ለማዘጋጀት ተመርጣለች" ብለዋል።


በተያያዘም የአፍሪካ ባሕል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ባሕል ስፖርቶች ፌዴሬሽን በቴክኒክ ድጋፍ፣ በሚዲያ አጠቃቀም፣ በባሕላዊ ጨዋታዎች ሕግጋት ዝግጅትና ሥልጠና ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0