በኦሮሚያ ክልል ሕገ-ወጥ የመኖሪያ ቤቶችን ወደ ሕጋዊ መስመር የሚያስገባ አዲስ ደንብ ጸደቀ
12:24 30.03.2026 (የተሻሻለ: 13:58 30.03.2026)

ሰብስክራይብ
በኦሮሚያ ክልል ሕገ-ወጥ የመኖሪያ ቤቶችን ወደ ሕጋዊ መስመር የሚያስገባ አዲስ ደንብ ጸደቀ
የከተማን ፕላን ለማስጠበቅ እና ዜጎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ ያለመው አዲሱ ደንብ ከ2005 ዓ.ም እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተገነቡ ሕገ-ወጥ ቤቶችን ብቻ የሚመለከት መሆኑን ክልሉ አስታውቋል።
በአዲሱ ደንብ መሠረት፦
በአንድ ከተማ ውስጥ ከአንድ ሕገ-ወጥ ግንባታ በላይ የሌለው ሰው መሆን ይገባል።
የሚሰጠው የቦታ ስፋት የከተማውን ዝቅተኛ መመዘኛ መስፈርት መሠረት ያደረገ ብቻ ይሆናል።
ሸገር፣ አዳማ እና ቢሾፍቱ ከተሞች ዘመናዊ የካዳስተር እና የዲጂታል የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ቀድመው በመተግበራቸው ይህ ደንብ በእነዚህ ከተሞች ላይ ተፈጻሚ አይሆንም።
የክልሉ መሬት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አሰፋ፤ "ሕገ-ወጥ ግንባታዎች ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርን ለመተግበር እንቅፋት በመሆናቸው፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት እና ከተሜነትን ለማረጋገጥ ደንቡ ጸድቋል" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X