የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በሩሲያ ባለሙያዎች የሚሰጠውን የድሮን ውጊያ ሥልጠና ጎበኙ

ሰብስክራይብ
የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት በሩሲያ ባለሙያዎች የሚሰጠውን የድሮን ውጊያ ሥልጠና ጎበኙ

ፎስተን አርካንጅ ቱዋዴራ በቤሬንጎ የሥልጠና ማዕከል በመገኘት በሩሲያ ወታደራዊ አሠልጣኞች ለሀገሪቱ የጦር ኃይሎች የሚሰጠውን ወታደራዊ ልምምድ መጎብኘታቸውን የሩሲያ የዓለም አቀፍ ደህንነት መኮንኖች ማኅበር አስታውቋል።

ሥልጠናው ትክክለኛ የውጊያ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ ሰው አልባ ተሽከርካሪዎችን ለስለላ እና ለውጊያ አገልግሎት ማዋል ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። በሩሲያ ባለሙያዎች መሪነት ሠልጣኞቹ በሚከተሉት ዘርፎች ብቃታቸውን አሳይተዋል፦

🟠 የድሮን ኦፕሬሽን፣
🟠 የአየር ቅኝት (ስለላ)፣
🟠 ተኩስ ማስተካከል፣
🟠 ስልታዊ የውጊያ ሁኔታዎች።

የፕሬዚዳንቱ ልዑክ የሩሲያ አሠልጣኞች ሥራ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክን ጦር የውጊያ አቅም ለማሳደግ እና የሀገሪቱን የመከላከል አቅም ለማጠናከር ቁልፍ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0