የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ፌኒቶይን መድኃኒት የጥራት ችግር አለበት በሚል በአስቸኳይ ከገበያ እንዲሰበሰብ አዘዘ
16:28 29.03.2026 (የተሻሻለ: 16:53 29.03.2026)

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ፌኒቶይን መድኃኒት የጥራት ችግር አለበት በሚል በአስቸኳይ ከገበያ እንዲሰበሰብ አዘዘ
የአገልግሎቱ የባህር ዳር ቅርንጫፍ፤ ሜዲካመን ባዮቴክ ሊሚትድ በተባለ ኩባንያ የተመረቱ የፌኒቶይን 100 ሚሊ ግራም ታብሌት መድኃኒቶች በሙሉ የጥራት ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ በአስቸኳይ እንዲሰበሰቡ ለሁሉም የጤና ተቋማት ትዕዛዝ አስተላልፏል።
አገልግሎቱ መድኃኒቱን ያልመለሱ የጤና ተቋማት ያላቸውን ቀሪ መጠን በደብዳቤ ገልጸው እስከ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንዲያሳውቁ ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠቱን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ይህንን ትዕዛዝ ተላልፈው መድኃኒቱን ተመላሽ የማያደርጉ ተቋማት ሙሉ ኃላፊነቱን እንደሚወስዱ የመድኃኒት አቅርቦት አገልግሎቱ አስጠንቅቋል።
ፌኒቶይን የሚጥል በሽታን ለመቆጣጠር የሚያገለግል መድኃኒት ነው።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X