የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ሊገነባ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.03.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ 40 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችን ሊገነባ ነው

አገልግሎቱ በአዲስ አበባ ከተማ ግንባታቸው ከተጠናቀቁ 6 ጣቢያዎች ውስጥ ሦስቱን በይፋ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል። በአዲስ አበባ ኮተቤ አካባቢ በ170 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ዘመናዊ የኃይል መሙያ ጣቢያ ትናንት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ጣቢያዎቹ በቀን 24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጡና የኃይል ጭነት በማይኖርበት ወቅት ተጠቃሚዎችን ለማበረታታት "በሚጠቀሙበት ጊዜ ላይ የተመሰረተ" ምክንያታዊ የዋጋ ተመን ተዘጋጅቶላቸዋል ተብሏል።


የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፤ “በመጀመሪያ ምዕራፍ በአዲስ አበባ 32 እንዲሁም በሌሎች ከተሞች 8 በድምሩ 40 መሙያ ጣቢያዎችን ለመገንባትና አገልግሎት ለማስጀመር አስፈላጊው ሥራ በመከናወን ላይ ነው” ብለዋል።


መሠረተ ልማቱ በቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ ባቱ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ ከተሞች እንደሚስፋፋና በኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ ኮሪደር አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0