የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ 'የደቡባዊ ዓለም ሀገራትን ሊያሰባስብ ይገባል' - ኢትዮጵያዊ ምሁር
14:31 29.03.2026 (የተሻሻለ: 17:52 29.03.2026)

ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ 'የደቡባዊ ዓለም ሀገራትን ሊያሰባስብ ይገባል' - ኢትዮጵያዊ ምሁር
ምዕራባውያን ሀገራት በመካከለኛው ምስራቅ ሆን ብለው አለመረጋጋትን በመፍጠር ቤቶችን የሚያፈርሱት ለተፈናቀሉት ሰዎች መጠለያ ለመንፈግ እንደሆነና "ሰብዓዊ መብት የሌላቸው ሰዎች" አድርገው እንደሚቆጥሯቸው አብዱ መሐመድ አሊ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የሰሜናዊ ዓለም ሀገራት ቀውሱን በሚከተሉት ነጥቦች ይዘውራሉ ሲሉም ምሁሩ አብራርተዋል፦
መፈናቀልን እንደ ጂኦፖለቲካዊ መሳሪያ መጠቀም፦ በታላላቅ ኃያላን ሀገራት መካከል በሚደረግ ፉክክር ግጭቶችን በማቀጣጠል ተራው ሕዝብ የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንዲሆን ማድረግ፣
ዓለም አቀፍ ሕግ "በምዕራባውያን ለምዕራባውያን"፦ የምዕራባውያንን ዓላማ ለማሳካት ብቻ ሕጉን እየመረጡ መተግበር፣
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት፦ "የዓለም አቀፍ ቀውስ ዋነኛ መሪዎች" በሆኑ አካላት መመራቱ፣
የመካከለኛው ምስራቅን የፖለቲካ ካርታ እንደገና የመሳል እቅዶች፡፡
ምሁሩ እንደ ብሪክስ ያሉ የበላይነትን የሚቋቋሙ ሚዛን ፈጣሪ ስብስቦች እንዲጠናከሩ ጥሪ አቅርበዋል።
"አሁን አዲስ ባለብዙ-ዋልታ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ከአንድ-ዋልታ ዓለም ወደ ብዙ-ዋልታ ዓለም እየተሸጋገርን ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X