ሴኔጋል አወዛጋቢውን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንሳይ ስታድ ደ ፍራንስ ስታዲየም ለእይታ አቀረበች

ሰብስክራይብ

ሴኔጋል አወዛጋቢውን የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ በፈረንሳይ ስታድ ደ ፍራንስ ስታዲየም ለእይታ አቀረበች

የቴራንጋ አንበሶች ቅዳሜ ዕለት ከፔሩ ጋር ያደረጉትን የወዳጅነት ጨዋታ ከመጀመራቸው በፊት ዋንጫውን ለደጋፊዎቻቸው ከፍ አድርገው አሳይተዋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የአሸናፊነቱን ክብር በይፋ ለሞሮኮ ቢሰጥም፤ የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን በጽኑ ተቃውሟል። ሴኔጋል ዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት በጉዳዩ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ዋንጫውን አልመልስም ብላለች።

ካፍ፤ በጥር ወር በራባት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ የሴኔጋል ተጫዋቾች ለ17 ደቂቃ ሜዳውን ጥለው በመውጣታቸው ጨዋታውን እንደተውት ቆጥሮ ድሉን 3 ለ 0 በኾነ የፎርፌ ውጤት ለሞሮኮ መስጠቱ ያታወሳል፡፡

ሴኔጋል ኒኮላስ ጃክሰን እና ኢስማኢላ ሳር ባስቆጠሯቸው ግቦች ፔሩን 2 ለ 0 አሸንፋለች። የቴራንጋ አንበሶች በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታ ፈረንሳይን ይገጥማሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0