🪖 ፔንታገን በኢራን ለሳምንታት የሚቆይ የምድር ዘመቻ ለማካሄድ እያጤነ መሆኑ ተነገረ

ፔንታገን
 ፔንታገን  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 29.03.2026
ሰብስክራይብ
🪖 ፔንታገን በኢራን ለሳምንታት የሚቆይ የምድር ዘመቻ ለማካሄድ እያጤነ መሆኑ ተነገረ

ፔንታገን በኢራን ልዩ ኃይል እና መደበኛ ወታደሮችን በማሳትፍ ለሳምንታት ሊቆይ የሚችል የምድር ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀ መሆኑን ዋሽንግተን ፖስት ነው የዘገበው። ይህ መረጃ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ቀጣናው እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ወቅት የመጣ ነው።

እቅዱ ወታደሮቹን ለኢራን ድሮኖች፣ ሚሳኤሎች እና ለምድር ተኩስ ተጋላጭ በማድረግ የግጭቱን ወደ አደገኛ ምዕራፍ መሸጋገር እንደሚያመለክት ዘገባው ጠቁሟል። ሆኖም ዶናልድ ትራምፕ እቅዱን ያጸድቁ እንደሆነ እስካሁን ግልጽ አይደለም።

ዘገባው ትራምፕ ቀደም ሲል "የትም ቦታ ወታደሮችን አላሰማራም"፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በበኩላቸው አሜሪካ "ያለ ምድር ጦር ሁሉንም ግቦቿን ማሳካት ትችላለች" ማለታቸውን አስታውሶ፤ ከዋሽንግተን የተጣረሱ መልዕክቶች እንደሚወጡ አመልክቷል።

ዘገባው የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ በዚህ ሳምንት ከኢራን ተወካዮች ጋር ድርድር እንደሚካሄድ ከገለጹ በኋላ የመጣ ነው። የኢራን ባለሥልጣናት ግን ከአሜሪካ ጋር የንግግር እቅድ እንደሌለ በመግለፅ ጉዳዩን አስተባብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0