በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች

በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች
በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.03.2026
ሰብስክራይብ
በ2017 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን አስተናግዳለች

አዲስ አበባ የዓለም አቀፍ ስብሰባዎች እና ጉባኤዎች ተመራጭ መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚንስትር ደኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገልጸዋል።

ሚኒስትር ደኤታው ይህን ያሉት በመጪው ሚያዝያ በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አኅጉራዊ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት በተዘጋጀ የገለጻ መድረክ ላይ ነው።

በመግለጫቸው እንዳመለከቱት፥ በዚህ ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ ከአምናው የበለጠ ቁጥር ኮንፈረንሶች በመዲናዋ ተካሂደዋል።


“ኢትዮጵያ ደግሞ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም አመቺ የሚያደርጋርጓት መሰረተ ልማቶችን፣ አዳራሾች፣ መሰብሰቢያ ማዕከላትን፣ ሆቴሎች የገነባች ሲሆን መስተንግዶው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው የሚገኘው። በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ነባር አዳራሾች ይበልጥ ታድሰዋል፣ አዳዲስ አዳራሾች ተገንብተዋል። በዚህ ምክንያት ብዙ አስቻይ የሆነ ሁኔታ አለ ማለት ነው።” ብለዋል።


የአፍሪካ አደጋ ስጋት አቅም አኅጉራዊ ኮንፈረንስ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መገለጹን የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0