የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መሥራቾች እና ባለቤቶች ላይ ክስ መሥርቻለሁ – ፖሊስ
18:19 28.03.2026 (የተሻሻለ: 18:47 28.03.2026)

ሰብስክራይብ
የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱ የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መሥራቾች እና ባለቤቶች ላይ ክስ መሥርቻለሁ – ፖሊስ
ዳንኤል ዮሃንስ ኢየሱስ እና ግርማይ ገ/ሚካኤል ይህደጎ የተባሉት የድርጅቱ ባለቤቶች፣ ከ1200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረስና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኙ ገንዘቦችን ሕጋዊ ማድረግን ጨምሮ በ19 ዓይነት የተለያዩ ወንጀሎች ዓቃቤ ሕግ ክስ እንደተመሠረተባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪ ዳንኤል ዮሃንስ ላይ ክስ ተመስርቶበት ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከታተል መደረጉንና ተጠርጣሪ ግርማይ ገ/ሚካኤልን ደግሞ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እያደረገ መሆኑንም ተገልጿል።
ድርጅቱን ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ በሕገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጋሪ በመሆን የተጠረጠሩ ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አብርሃም ግዛው፣ ይገረም ደጀኔ፣ መንሱር ጀማል እና ካሊድ ናስር የተባሉ ታዋቂ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎችንም ፍርድ ቤት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው ፍርድ ቤትም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም መፍቀዱ ገልጿል፡፡
የማስታወቂያ ባለሙያዎቹ እያንዳንዳቸው 8 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የ"ቢዋይዲ ሶንግ ፕላስ" መኪና በስጦታ በመቀበል በወንጀልም ተጠርጥረዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X