ባርነትን በሰብአዊነት ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል እውቅና መስጠት ተጠያቂነትን ያስከትላል፣ ሆኖም ዐሻራው አሁንም ቀጥሏል - የቡርኪና ፋሶ ባለሙያዎች
15:55 28.03.2026 (የተሻሻለ: 16:50 28.03.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ባርነትን በሰብአዊነት ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል እውቅና መስጠት ተጠያቂነትን ያስከትላል፣ ሆኖም ዐሻራው አሁንም ቀጥሏል - የቡርኪና ፋሶ ባለሙያዎች
የባርነት ታሪክ የተጻፈው የሙግት መድረኮችን አሁንም መሸሽ በሚፈልጉ የቀድሞ ቅኝ ገዥ ኃይላት መሆኑን ፖል ኡስማን ኮምፓኦሬ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
“አፍሪካ አሁን ላይ የራሷን ታሪክ መናገርና ለታሪክ መዝገቦቿ ዋጋ መስጠት አለባት። የራሷን ተመራማሪዎች ማሰልጠን ይኖርባታል። ለረጅም ጊዜ ታሪካችን ሲጻፍ የቆየው በቀኝ በገዙንና በጨቆኑን ኃይላት ነው” ብለዋል።
በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ፍትህ እንዲሰፍን የሚከተሉትን ነጥቦች አሳስበዋል፦
የባርነት ታሪክ በትምህርት መልክ እንዲሰጥ፣
የኢኮኖሚ ካሳ እንዲከፈል እና
በሕዝቦች መካከል እኩልነት ያለው ግንኙነት እንዲመሠረት።
የተባበሩት መንግሥታት ባርነትን በሰብአዊነት ላይ እንደተፈጸመ ወንጀል በይፋ ቢያውጅም፣ ውጤቱ ግን አሁንም ድረስ በመላው አኅጉሪቱ እየታየ መሆኑን ፕሮፌሰር ኢድሪሳ ኦውድራጎ አጽንዖት ሰጥተዋል።
“ይህ ድርጊት በአፍሪካ አገራትና በቀድሞ ቅኝ ገዥዎች መካከል ያለው የሀብት ክፍተትና አለመመጣጠን እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል። በአንድ በኩል ከፍተኛ የሀብት ክምችት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዘላቂ አቅመ ደካማነት እንዲፈጠር አድርጓል” ብለዋል።
እንዲህ ዓይነቱ ተምሳሌታዊ እውቅና፣ በተግባራዊ እርምጃዎች፣ በካሳ ክፍያ እና በይፋዊ ይቅርታ ሊታጀብ እንደሚገባ በማሳሰብ ደምድመዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X