በ19ኛው ክፍለ ዘመን በብሪታንያ ወታደሮች ተዘርፎ የነበረው የእቴጌ ጥሩወርቅ የወርቅ ፀጉር ጌጥ በክብር ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

ሰብስክራይብ
በ19ኛው ክፍለ ዘመን በብሪታንያ ወታደሮች ተዘርፎ የነበረው የእቴጌ ጥሩወርቅ የወርቅ ፀጉር ጌጥ በክብር ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ

ከወርቅ የተሠራው ይህ የፀጉር ማስያዣ (ሻጤ) የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ባለቤት እቴጌ ጥሩወርቅ መሆኑን "ሮያል ኢትዮጵያ ትረስት" ከዚህ ቀደም አስታውቋል፡፡

በቅርስ ርክክብ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬከተር አበባው አያሌው፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ውጭ የተወሰዱ ከ72 በላይ ቅርሶችን ማስመለስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ፣ የኢትዮጵያ ንጉሳዊ በጎ አድራጎት ባለ አደራ ድርጅት ይህንን ቅርስና ከዚህን በፊትም የአጼ ተዎድሮስ ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ሲሉ ለድርጅቱ፣ ለልዑል ኤርሚያስ ሳሕለሥላሴ እና ለአሉላ ፓንክረስት (ዶ/ር) ምስጋና ማቅረባቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

ቪዲዮው፦ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ተወካዮችና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የተደረገውን የርክክብ ሥነ-ስርዓት ያሳያል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0