‘አሁኑኑ ካሳ ይከፈል!’ የብራዚል ሚኒስትር የተመድን የባርነት ውሳኔ ተከትሎ ምላሽ ሰጡ

የብራዚል ሚኒስትር የተመድን የባርነት ውሳኔ ተከትሎ ምላሽ ሰጡ
የብራዚል ሚኒስትር የተመድን የባርነት ውሳኔ ተከትሎ ምላሽ ሰጡ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.03.2026
ሰብስክራይብ
‘አሁኑኑ ካሳ ይከፈል!’ የብራዚል ሚኒስትር የተመድን የባርነት ውሳኔ ተከትሎ ምላሽ ሰጡ

​ባርነት በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ አስከፊ ወንጀል መሆኑ መታወቁ ትልቅ መሻሻል ቢሆንም፣ በተግባር የተደገፈ እርምጃ ካልታከለበት ግን በቂ አይደለም ሲሉ የብራዚል የዘር እኩልነት ሚኒስትር አኒዬል ፍራንኮ አፅንዖት ሰጥተዋል።
​

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ፣ "የዘር ዕኩልነት ፍትሕ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን ብቻ ሆኖ መቅረት የለበትም። ይልቁንም የመንግሥት ፖሊሲ ሊሆን ይገባል" ብለዋል።


​እንደ ፍራንኮ ገለፃ፣ በብራዚል የዘር እኩልነትን ለማስፈን የቀረቡት እንደ ፒኢሲ 27 ያሉ የሕገ-መንግስት ማሻሻያ ሀሳቦች እና የብራዚል ብሔራዊ የዘር እኩልነት ማሳደጊያ ሥርዓት መጠናከር ለጥቁር ህዝቦች ቀጣይነት ያለው ካሳ ለመክፈል መንገዱን ያሳያሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0