ናይጄሪያ የንፁህ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲያካትት አደረገች - የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት

ናይጄሪያ የንፁህ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲያካትት አደረገች
ናይጄሪያ የንፁህ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲያካትት አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.03.2026
ሰብስክራይብ
ናይጄሪያ የንፁህ ትራንስፖርት እንቅስቃሴዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲያካትት አደረገች - የፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት

​ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ቀደም ሲል "የፕሬዝዳንታዊ የተፈጥሮ ጋዝ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ተነሳሽነት" ብለዉ አዲስ ስያሜ የሰጡትን መርሃ ግብር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችንም እንዲያካትት መፍቀዳቸውን የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ ባዮ ኦናኑጋ አስታውቀዋል።

​ይህ ተነሳሽነት አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የናይጄሪያን የንፁህ ትራንስፖርት ስትራቴጂ የሚያስተባብር ሲሆን፣ በጋዝ የሚሰሩ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም እንደ ጋዝ መሙያ እና የኤሌክትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ያሉ መሠረተ ልማቶችን በበላይነት ይቆጣጠራል።

​ የተሽከርካሪ ለውጥ ሂደት ለሁሉም ተደራሽ እንዲሆን፣ ፕሬዝዳንቱ ተነሳሽነቱ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን አነስተኛ ወጪ ያላቸው የብድር አማራጮችን እንዲያመቻች መመሪያ ሰጥተዋል። በተጨማሪም ቋሚ መሠረተ ልማቶች እስኪገነቡ ድረስ ተንቀሳቃሽ የጋዝ መሙያ ክፍሎችን ስርጭት ለማፋጠን ታቅዷል።

​እ.ኤ.አ. በ2023 የነዳጅ ድጎማ መነሳቱን ተከትሎ የመጣውን ጫና ለመቀነስ የተጀመረው ይህ መርሃ ግብር፣ የናይጄሪያን የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በመጠቀም የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ፣ የኃይል ዋስትናን ለማጠናከር እና ከውጭ በሚገባ ነዳጅ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ያለመ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0