"ኢራንን ክፉ አድርጎ በመሳል ከጎረቤቶቿ ጋር የማጋጨት ዘመቻ እየተካሄደ ነው" - የፖለቲካ ተንታኝ
19:47 26.03.2026 (የተሻሻለ: 20:21 26.03.2026)

ሰብስክራይብ
"ኢራንን ክፉ አድርጎ በመሳል ከጎረቤቶቿ ጋር የማጋጨት ዘመቻ እየተካሄደ ነው" - የፖለቲካ ተንታኝ
አሜሪካ እና እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ኢራንን ለብቻዋ ነጥሎ ለመምታት እና ቀጣናዊ ተጽዕኖዋን ለማዳከም የፓለቲካ አሻጥር እየሠሩ ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኝ መሐመድ ሰይድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
"ኢራን ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን ዝምድና በመበጠስ፣ በማንነቷም ሆነ በሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ተነጥላ እንድትኖር የታለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።"
ይህም ኢራን በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና ለማዳከም እና በአሜሪካ ተጽዕኖ ስር ባሉ ሀገራት ቁጥጥር ስር እንድትወድቅ የታለመ እንቅስቃሴ መሆኑንም ተንተኙ አንስተዋል።
“ኢራን አረብ አለመሆኗን (ፋርስ መሆኗን) እና የሃይማኖት ክፍሎችን እንደ ግብዓት በመጠቀም፣ ጎረቤቶቿ በጥርጣሬ እንዲመለከቷትና የጦርነት አዋጅ እንዲያውጁባት የመቀስቀስ ስራ እየተሰራ ነው” ብለዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል የኢራንን ድሮኖች የሚመስሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ጥቃቶችን በማድረስ አለመተማመኑን ለመፍጠር እየሠሩ መሆኑን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X