የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የቀደምት አባቶች አፅም ዳግም ቀብር "ለዘመናት የዘለቀው ህመም ማብቂያ" ነው ሲል ገለፀ
19:23 26.03.2026 (የተሻሻለ: 19:24 26.03.2026)
ሰብስክራይብ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የቀደምት አባቶች አፅም ዳግም ቀብር "ለዘመናት የዘለቀው ህመም ማብቂያ" ነው ሲል ገለፀ
የ63 የኮይ እና የሳን ተወላጆች አፅም ወደ ሀገራቸው ተመልሶ በክብር እንዲያርፍ መደረጉ "በቅኝ ግዛት ወረራ ወቅት የደረሰውን ውርደት ለመካስ ወይም ለመጠገን" ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌንያ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አክለውም፣ ቀደም ሲል የተፈጸሙ ግፎች ፍጹም ስህተት እንደነበሩ በሞራል ደረጃ ከማመን ባለፈ፤ እንደ "ካሳ" የሚቆጠሩ የሁለትዮሽ የማስተካከያ እርምጃዎች ሊከተሉ እንደሚገባ ገልጸዋል።
"ይህ ጉዳይ በፕሬዝዳንቱ እይታ እንደ አንድ የህግ ሂደት ብቻ የሚታይ ሳይሆን፣ በሁለትዮሽ ደረጃ ሊመከርበትና መፍትሄ እንዲሁም ካሳ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው" ሲሉ ማግዌንያ አሳስበዋል።
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ፣ የደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ ፕሮግራም የቅኝ ግዛት እና የአፓርታይድን ጠባሳዎች ለመፈወስ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ይሰራል፦
የባህል ማንነት እና የቋንቋ መጥፋት፣
ከቀዬ መፈናቀል እና
የባህል ቅርሶችን ያለአግባብ መውሰድ (ምዝበራ)።
"እውቅና መስጠት ተጨባጭ መሆን አለበት፡፡ ተግባራዊ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ትርጉም ያለው መሆን አለበት፡፡ ዝም ብሎ ባዶ ቃላት ብቻ ሊሆን አይችልም" ሲሉ አፅንዖት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X