የማዱሮ ችሎትን ለመከታተል በርካታ ሰዎች በኒውዮርክ ተሰበሰቡ

ሰብስክራይብ

የማዱሮ ችሎትን ለመከታተል በርካታ ሰዎች በኒውዮርክ ተሰበሰቡ

የቬንዙዌላው ፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ ሁለተኛ የፍርድ ቤት ውሎ ከመጀመሩ በፊት፣ በማንሃተን የፌዴራል ፍርድ ቤት ደጃፍ ጋዜጠኞችን፣ የፕሬዝዳንቱን ደጋፊዎችን እና ችሎቱን ለመታደም የሚፈልጉ ሰዎችን ጨምሮ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ( በኢትዮጵያ 8፡00 ሰዓት) ጀምሮ ተሰብስበዋል።

የችሎቱ ሂደት በዳኛ አልቪን ሄለርስቲን ሰብሳቢነት በአካባቢው አቆጣጠር ከረፋዱ 5:00 ሰዓት (በኢትዮጵያ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት) ላይ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

በችሎቱ ለመገኘት ያለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ፣ አንዳንዶች ወረፋ ለመያዝ በሰዓት 50 ዶላር ሲጠይቁ ተስተውሏል።

ፕሬዝዳንት ማዱሮ እና ባለቤታቸው ጥር 3 ቀን በቬንዙዌላ መዲና ካራካስ በተደረገ ወረራ በአሜሪካ ወታደሮች በእገታ ከተያዙ በኋላ፣ በብሩክሊን እስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ።

በዕፅ ዝውውር የታገዘ ሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት ፕሬዝዳንቱ፣ በጥር ወር በነበራቸው የመጀመሪያ ችሎት፦ “እኔ ጥፋተኛ አይደለሁም፤ እኔ የተከበርኩ ሰው ነኝ። አሁንም የሀገሬ ፕሬዝዳንት ነኝ” በማለት የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0