የመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት በአሜሪካ የደህነት ዋስትና ስር ወድቀዋል - ባለሙያ
17:33 26.03.2026 (የተሻሻለ: 17:39 26.03.2026)

ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ የአረብ ሀገራት በአሜሪካ የደህነት ዋስትና ስር ወድቀዋል - ባለሙያ
ሀብት ኖሮህ መከላከያህ ካልጠነከረ በርህን ከፍተህ እንደመቀመጥ መሆኑን የቪኦኤ (ድምፅ ለሁላችን) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሥራችና የፖለቲካ ተንታኝ መሐመድ ሰይድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡
"አረብ ሀገራት ሉዓላዊነታቸውን በአሜሪካ ፈቃድ ላይ ጥለውታል። አሜሪካ የፈለገች እለት የምታደርገውና የምታቆመው የጸጥታ ጥበቃ ሀገራቱን ለከፍተኛ ስጋት አጋልጧቸዋል።"
አብዛኞቹ የአረብ ሀገራት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አሜሪካ ውስጥ ኢንቨስት ማድረጋቸውን ያብራሩት መሐመድ፣ ለራሳቸው ግን ጠንካራ የመከላከያ ቴክኖሎጂ መገንባት እንደተሳናቸው አንስተዋል።
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከግጭት ወጥመድ ለመውጣት ያላቸው የተሻለው መንገድ ቀጣናዊ ውህደት ነው ያሉት ተንታኙ ፤ የኢኮኖሚ ትስስር ፖለቲካዊ አንድነትን ስለሚያመጣ የውጭ ጣልቃ ገብነትን ይቀንሳል ሲሉ ምክረ ሀሳባቸውን አስቀምጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X