በአሰቃቂ የጅብ ጥቃት ከፍተኛ የፊት አካል ጉዳት የደረሰበት ሕጻን ከስኬታማ 8 ቀዶ ሕክምናዎች በኋላ ዳነ
12:39 26.03.2026 (የተሻሻለ: 13:19 26.03.2026)

ሰብስክራይብ
በአሰቃቂ የጅብ ጥቃት ከፍተኛ የፊት አካል ጉዳት የደረሰበት ሕጻን ከስኬታማ 8 ቀዶ ሕክምናዎች በኋላ ዳነ
ታዳጊው በአለርት ኮፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተደረገለት ውስብስብ ቀዶ ሕክማና አዲስ ተስፋ ማግኘቱን ሆስፒታሉ ለአገር ውስጥ ሚዲያ አስታውቋል።
ሕጻኑ በጥቃቱ ምክንያት ሁለቱንም ዓይኖቹን ያጣ ሲሆን፣ በግንባሩ፣ በጉንጮቹ እና በላይኛው መንጋጋው ላይ የነበሩ አጥንቶችና ቆዳዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር ተብሏል።
በዚህም የቀድሞ ገፅታው ለመመለስ በተደረገው የቀዶ ሕክምና ሕጻኑ ጭን ላይ 17 ሳ.ሜ ርዝመት ያለው ቆዳና ስጋ ከነደምስሩ በመውሰድ በፊቱ ላይ በተሳካ ሁኔታ መተከሉ ተገልጿል።
ሕጻኑ መተንፈስ እንዲችል በአንገቱ በኩል ቀዳዳ የተከፈተ ሲሆን የተሰባበሩ የመንጋጋ አጥንቶች በታይታኒየም ፕሌትና ስክሩ ተደግፈው የፊት ቅርጽ እንዲይዙ ተደርጓል።
እስካሁን 8 ቀዶ ሕክምናዎች የተደረጉለት ሲሆን፣ የሆስፒታሉ በርካታ ስፔሻሊስቶች፣ የማደንዘዣ ባለሙያዎች እና ነርሶች የተሳተፉበት የተቀናጀ ቡድን የሕጻኑን ሕይወት ታድጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X