የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ በአፍሪካ "የሸቀጦች እጥረት መከሰቱ የማይቀር ነው" - ሴኔጋላዊ ባለሙያ

በአፍሪካ "የሸቀጦች እጥረት መከሰቱ የማይቀር ነው"
በአፍሪካ የሸቀጦች እጥረት መከሰቱ የማይቀር ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.03.2026
ሰብስክራይብ
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት፦ በአፍሪካ "የሸቀጦች እጥረት መከሰቱ የማይቀር ነው" - ሴኔጋላዊ ባለሙያ

በመካከለኛው ምስራቅ የሚቀጥለው ግጭት ለድሃ የአፍሪካ ሀገራት የሚያስከትለው መዘዝ ስር የሰደደ (መዋቅራዊ) እንደሚሆን የሴኔጋል የነጋዴዎች እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኡማር ሲሴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

እንደ ባለሙያው ገለፃ ከሆነ የነዳጅ ዋጋ እጥፍ መጨመር አሁን ላይ የማይቀር የዋጋ ግሽበትን የቀሰቀሰ ቢሆንም፣ ዋናው ስጋት ግን የሸቀጦች አለመኖር ነው።


«እነዚህ ክምችቶች ቢበዛ ለሁለት ወይም ለሦስት ወራት ብቻ የሚቆዩ እንጂ ብዙ ጊዜ የሚዘልቁ አይደሉም» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።


አኅጉሪቱ የምትጠቀማቸው 90 በመቶ የሚሆኑት ሸቀጦች ከውጭ የሚገቡ በመሆናቸው፣ ሀገራቱ ለውጭ ተጽዕኖዎች ተጋላጭ መሆናቸው ሁኔታውን ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል።


«ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ ይቆማል ብለን ተስፋ እናድርግ፤ ካልሆነ ግን ሁሉም ሰው ይሰቃያል። በተለይም ደግሞ በጣም ደሃ የሆኑት የእኛ ሀገራት» ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል።


በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0