በሕንድ ለኢትዮጵያዊ የኤች.አይ.ቪ. ታማሚ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተከናወነ
21:10 25.03.2026 (የተሻሻለ: 21:34 25.03.2026)
ሰብስክራይብ
በሕንድ ለኢትዮጵያዊ የኤች.አይ.ቪ. ታማሚ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ተከናወነ
በሕንድ ዴልሂ የሚገኘው 'ማክስ ሱፐር ስፔሻሊቲ' ሆስፒታል ኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ በደሙ ውስጥ ለሚገኝ የ43 ዓመት ኢትዮጵያዊ እጅግ ስኬታማ የሆነ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጉን አስታውቋል።
ይህ የህክምና ሂደት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ለሚገኝ ሰዎች ንቅለ ተከላ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር ያሳየ በመሆኑ በዘርፉ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል፡፡
🫀ለንቅለ ተከላው ስኬታማነት ዘመናዊ የፀረ-ሬትሮ ቫይረስ ህክምናዎች እና በጥንቃቄ የተመራ የበርካታ የህክምና ባለሙያዎች ቅንጅት ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ይህ ስኬት በኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ የተያዙ እና የኩላሊት ህመም ያለባቸው ታማሚዎች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑ ተገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X