የባርያ ንግድ ዓሻራ እና የመከላከያ መንገዶቹ፦ የኬንያዊቷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እይታ

ሰብስክራይብ

የባርያ ንግድ ዓሻራ እና የመከላከያ መንገዶቹ፦ የኬንያዊቷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እይታ

በምስራቅ አፍሪካ የአትላንቲክ ማዶ የባርነት ንግድ ከስነ-ልቦና አንጻር የራቀ መስሎ ይታያል ሲሉ የ‘ጄኤም-ቃፍሪ ሜቱሴላ’ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ክሌር አቲየኖ ኦቲይኖ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። ይህን ያሉትም ዓለም አቀፍ የባርነት እና የአትላንቲክ ማዶ የባርነት ንግድ ሰለባዎች መታሰቢያ ቀንን አስመልክቶ ነው።

ይሁን እንጂ የአትላንቲክ የባርነት ንግድ የአፍሪካን እድገትና ልማት ወደኋላ መጎተቱን ገልጸው፤ እስካሁን ድረስ የሚቀጥሉ በርካታ መዘዞችን ጠቅሰዋል፦

የሰው ኃይል መመዝበሩ የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ እድገት ገድቧል፡፡

ያልተከፈለበት ጉልበት የምዕራባውያንን ሀብት ሲያሳድግ፣ እስከ ዛሬ የሚቀጥል የሀብት ልዩነት ፈጥሯል፡፡

ስለ ባርያ ንግድ መዘዞች እና መፍትሄዎች የሚያስተምር የትምህርት ስርዓት እጥረት አሁንም አለ።

ኦቲየኖ "አሁን በአፍሪካ ውስጥ እየታየ ባለው ልማት ላይ ትኩረት ማድረግ" አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተዋል።

"አሁን ላይ በጣም ምክንያታዊ የሚሆነው በግብርና፣ በማዕድን እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ድንበር ተሻጋሪ የጋራ ማኅበራት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው፤ [...] የአፍሪካ ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ ባለበት በዚህ ወቅት የምዕራባውያን ተጽዕኖ እየተዳከመ ነው" ሲሉ ባለሙያዋ ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0