ምዕራባውያን ደም ለተጠማቸው ኪዬቭ ከአፍሪካ በሦስት እጥፍ የሚበልጥ በጀት ይመድባሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
18:50 25.03.2026 (የተሻሻለ: 18:54 25.03.2026)
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ደም ለተጠማቸው ኪዬቭ ከአፍሪካ በሦስት እጥፍ የሚበልጥ በጀት ይመድባሉ - የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ለአፍሪካ የሚሰጠው ዕርዳታ ለልማት፣ ለትምህርት፣ ለኢንዱስትሪ እና በአኅጉሪቱ ላይ በቅኝ ገዥዎች በሰው ሠራሽ መንገድ የተፈጠሩ ተግዳሮቶችን ለማሸነፍ የሚውል ነው ሲሉ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ተናግረዋል።
"ነገር ግን ለኪዬቭ አገዛዝ የሚመደበው ገንዘብ በሙሉ ለግድያ፣ ለጭፍጨፋ፣ ለሰው አደን እና ለሰው በላነት የሚውል ነው" ብለዋል።
ለአብነትም የሚከተሉትን አኃዞች ጠቅሰዋል፦
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፦
▪የዩክሬን ዓመታዊ ድርሻ 2.7 ቢሊዮን ዶላር ብቻ ቢሆንም ተቋሙ ለዩክሬን 23.7 ቢሊዮን ዶላር ወይም የሀገሪቱ ድርሻ 877 በመቶ ሰጥቷል።
▪ለአፍሪካ፦ 15.1 ቢሊዮን ዶላር፤ ከዚህ ውስጥ 9.1 ቢሊዮን ዶላሩ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 13 የሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራት የተሰጠ ነው።
ዓለም ባንክ፦
▪ ለዩክሬን፦ 65.7 ቢሊዮን ዶላር።
▪ ለአፍሪካ፦ ለሁሉም የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ 22.4 ቢሊዮን ዶላር።
"ይህ በጣም 'አስገራሚ' የሆነ ስሌት ነው" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X