ኢትዮጵያ በምግብ ራስን የመቻል አቅሟን ለማሳደግ ሀገራዊ የማሽላ ልማት ንቅናቄ ይፋ አደረገች
18:12 25.03.2026 (የተሻሻለ: 18:37 25.03.2026)
© Sputnik
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በምግብ ራስን የመቻል አቅሟን ለማሳደግ ሀገራዊ የማሽላ ልማት ንቅናቄ ይፋ አደረገች
ይህ ሀገራዊ የማሽላ ልማት ፕሮግራም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለመቀነስ እና ለአግሮ-ኢንዱስትሪ ዕድገት ግብዓት ሆኖ እንደሚያገለገል የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፣ ይህ ተነሳሽነት ዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ ንረትን ለመቋቋም እና ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የመጣውን ከፍተኛ ፍላጎት ለማሟላት ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።
"በቴክኖሎጂ የታገዘ ምርትን በማስፋፋት የዶሮ መኖ እና የመጠጥ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ ታቅዷል” ብለዋል።
ይህ ፕሮግራም ማሽላን ከኢንዱስትሪ ልማት ጋር በማሰናሰል የገጠር አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ ተገልጿል።
አርሶ አደሮች፣ ተመራማሪዎች እና የልማት አጋሮችን በማሳተፍ በአዲስ አበባ በተካሄደ ወርክሾፕ የ"ማሽላ ፍላግሺፕ ፕሮግራም" በይፋ ፀድቋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X