"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የታማኝነት ቀውስ ውስጥ ነው" - የሕግ ባለሙያ

የወንጀለኞች ፍርድ ቤት
የወንጀለኞች ፍርድ ቤት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.03.2026
ሰብስክራይብ
"ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የታማኝነት ቀውስ ውስጥ ነው" - የሕግ ባለሙያ

ተቋሙ በምዕራባውያን የፖለቲካ እና የፋይናንስ ተፅዕኖ ስር በመውደቁ "ድርብ መስፈርት" (ለሁሉም በኩል የማይሰራ) እየተከተለ መሆኑን የሕግ ባለሙያው ዳንኤል ፍቃዱ ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።


"ፍርድ ቤቱ በዩክሬን ጉዳይ የሮም ስምምነት ፈራሚ ባትሆንም እንኳ በፍጥነት ጣልቃ ገብቷል፤ በጋዛ እና በኢራን ላይ ግን አባል አይደሉም በሚል ምክንያት ዝምታን መርጧል። ይህ ግልጽ የሆነ የፖለቲካ አድሏዊነት ነው" ብለዋል።


የፍርድ ቤቱ ዋና መቀመጫና የገንዘብ ምንጭ ምዕራባውያን በመሆናቸው፣ በታላላቅ ኃያላን ሀገራት የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመመርመር የሞራል ብቃት እንደሌለው ባለሙያው አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት እንደ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ያሉ ሀገራት ከተቋሙ ለመውጣት መወሰናቸው የፍርድ ቤቱ መዳከም ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0