በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው የገጠር ሞዴል መንደር
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ ውስጥ በገጠር ኮሪደር ልማት ተነሳሽነት የተገነባው የገጠር መንደር አካባቢውን እና ሕብረተሰቡን ከመሠረተ ልማት ጋር ያስተሳስራል፡፡
ሁሉንም መሠረተ ልማቶች በአንድ አካባቢ አስተሳስሮ በማሟላት የገጠሩን ማኅበረሰብ የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ያለመ ነው። በዚህም፦
የመንገድ፣
የኤሌክትሪክ፣
የንጹሕ መጠጥ ውኃ፣
የትምህርት፣
የጤና እና
የግብርና (የዶሮና የንብ ማርቢያ እና የእንስሳት በረት) አቅርቦቶችን አሟልቷል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት በይፋ አገልግሎት የጀመሩት መኖሪያ ቤቶቹ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ (ፈርኒቸር) ተሟልቶላቸዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X