የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት ባንኮች ጥምረት መቀላቀሉን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት ባንኮች ጥምረት መቀላቀሉን አስታወቀ
ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት ባንኮች ጥምረት መቀላቀሉን አስታወቀ   - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.03.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓለም አቀፉን የልማት ባንኮች ጥምረት መቀላቀሉን አስታወቀ

ባንኩ ከ530 በላይ የመንግሥታዊ የልማት ባንኮችን ያቀፈውንና 23 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋ ንብረት የሚያንቀሳቅሰውን ግዙፉን የ"ፋይናንስ ኢን ኮመን" (FiCS) ጥምረት በይፋ ተቀላቅሏል።

የዚህ አባልነት ዋና ዋና ጥቅሞች፡-

የእውቀትና ተሞክሮ ልውውጥ፦ ከዓለም አቀፍ ባንኮች የተሰበሰበና የተቀመረ እውቀት፣ ልምድ እና ተሞክሮ ለማግኘት ያስችለዋል፡፡

ተጨማሪ የፋይናንስ ዕድሎች፦ አካታችና ምቹ የሆኑ የልማት ፋይናንሶችን የማግኘት ዕድልን ያሰፋል፡፡

ዓለም አቀፍ ትብብር፦ በአየር ንብረት እና በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፋይናንስ አካታችነት ዙሪያ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር በጋራ የመሥራት ዕድል።

የፈጠራ ማዕከላት ተጠቃሚነት፦ በጥምረቱ ስር በሚገኙ የሐሳብ ማመንጫ (Innovation Lab) እና የዋስትና ማዕከላት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ይችላል።

ተቋማዊ ዝና፦ የባንኩን ዓለም አቀፍ ታማኝነት፣ ዝና እና ተቀባይነት በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0