በጎንደር ከተማ የተገነቡ የገጠር ኮሪደር ሞዴል ቤቶች ተመረቁ
ም/ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በከተማዋ ሳይና ሳቢያ የገጠር ቀበሌ የጤና ጣቢያ፣ የመብራትና የውኃ አገልግሎትን አካቶ የተገነባውን የሞዴል መንደር መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል፡፡
የሞዴል መንደሩ በአንድ ወር የግንባታ ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁን የገለፁት ሚኒስትሩ የሰዎች መኖሪያን ከእንስሳት መጠለያ በመለየት ለጤናማና ለሥልጡን አኗኗር መሠረት ጥለናል ብለዋል።
“ጎንደር ከተማዋ ብቻ ሳይሆን ገጠሩም በኮሪደር ልማት አዲስ የታሪክና የሥልጣኔ ምዕራፍ ተከፍቶለታል” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
ተመስገን ጥሩነህ አክለውም፤ የገጠር ኮሪደሩ ዙሪያውን በተቀናጀ የሌማት ትሩፋት የታጀበና ፣ አርሶ አደሩን የዘመናዊነትና የምርታማነት ባለቤት የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X