የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚጀምር ተገለፀ

ሰብስክራይብ

የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እስከ ሚያዚያ ወር መጨረሻ ድረስ በመዲናዋ ሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚጀምር ተገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውንና ሦስተኛውን የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት መስጫ ማዕከልን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ተጨማሪ ሦስት ማዕከላት በመጋቢት ወር ቀሪ ቀናት የሚከፈቱ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ፤ እስከ ሚያዚያ መጨረሻ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚጀመር አስታውቀዋል።

አገልግሎት መስጠት በጀመሩት የአራዳና ቦሌ ክፍለ ከተሞች የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ከ120 ሺህ በላይ ዜጎች አገልግሎት ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

አዲስ መሶብ ዜጎች በአገልግሎት ምክንያት የሚደርስባቸውን እንግልት፣ የጊዜና የጉልበት ብክነት ከማስቀረት አንፃር መሠረታዊ ለውጥ እያስገኘ መሆኑን ከንቲባዋ ጠቅሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0