በሚያዝያ ወር በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ከፍተኛ ዝናብና ሞቃታማ የአየር ጸባይ እንደሚጠበቅ ተነገረ
20:57 24.03.2026 (የተሻሻለ: 21:04 24.03.2026)
ሰብስክራይብ
በሚያዝያ ወር በኢትዮጵያና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ከፍተኛ ዝናብና ሞቃታማ የአየር ጸባይ እንደሚጠበቅ ተነገረ
ከመጪው ሚያዝያ እስከ ሰኔ 2026 ባሉት ወራት በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ ከፍተኛ ዝናብ እንዲሁም ሞቃታማ የአየር ጸባይ እንደሚከሰት የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል አስታውቋል።
በትንበያው መሠረት፦
በኢትዮጵያ አብዛኛው አካባቢ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳና ታንዛኒያን ጨምሮ በአብዛኛው የቀጣናው ሀገራት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይጠበቃል።
በሰሜናዊ ሶማሊያ፣ በደቡባዊ ኤርትራ እንዲሁም በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች መደበኛና ከመደበኛ በታች የሆነ ደረቅ የአየር ጸባይ ሊታይ ይችላል።
በሱዳን፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲና በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ከመደበኛው የላቀ ከፍተኛ ሙቀት እንደሚመዘገብ ተተንብይዋል።
በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች፣ በኬንያና በታንዛኒያ መደበኛና ቀዝቃዛማ የአየር ጸባይ ሊከሰት እንደሚችል ማዕከሉ አመልክቷል።
በአጠቃላይ በሚያዝያ ወር የሚታየው የአየር ንብረት በከፍተኛ ዝናብና በሙቀት መካከል የሚቀያየር "ድብልቅ" የአየር ሁኔታ እንደሚሆን ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X