- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ሁለት የልማት ግንባሮች፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መዋጋትና ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት

ሁለት የልማት ግንባሮች፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታን መዋጋትና ጠንካራ ኢኮኖሚን መገንባት
ሰብስክራይብ
"አብዛኞቹ ለቲቢ የምንጠቀማቸው መድኃኒቶች ከውጭ የሚገቡ ናቸው። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስወጣናል። ለውጭ ተፅዕኖ ተጋላጭ የሆንነውም ለዚህ ነው። ስለዚህ፣ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን የምናጎለብትበት ዕድል ካገኘን፣ የገንዘብ ድጋፍ ቅነሳ የሚያስከትለውን ችግር መቋቋም እንችላለን። ለአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች የራሳቸውን የምርመራ መሣሪያዎችና መድኃኒቶች ማምረት እንዲችሉ አቅማቸውን ማጠናከር ይገባል።" ሲሉ የ 'ቮለንተሪ ሄልዝ ሰርቪስ' ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በቀዳሚነት ዛሬ መጋቢት 15 ቀን የሚከበረውን የዓለም የሳንባ ነቀርሳ ቀንን በማሰብ በሩሲያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሳንባ ነቀርሳ ዋና አማካሪ ስፔሻሊስት ከሆኑት ከኢሪና ቫሲሊየቫ እንዲሁም የቪ.ኤች.ኤስ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከአቶ እንዳልካቸው ፍቃዱ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የሳንባ ነቀርሳ ከድህነት፣ ከጤና ሥርዓት እና ከማኅበራዊ እውነታዎች ጋር እንዴት እንደሚገናኝ እንቃኛለን፤ በማስከተልም፣ ከመጋቢት 15 እስከ 17፣ 2018 ዓ.ም በሚካሄደው 10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲ ፍሎራ ኤክስፖ ላይ ተገኝተን ከኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ እና ከአቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራቾችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዘርፉ ለኢኮኖሚው ያለውን ሚና እንዳስሳለን፡፡
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ : Apple PodcastsSpotifyDeezerAfripodsPodcast AddictPocket CastsCastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0