የኢትዮጵያ ባሕላዊ መድኃኒቶች ወደ ፋብሪካ ምርት ሊሸጋገሩ ነው

የኢትዮጵያ ባሕላዊ መድኃኒቶች
የኢትዮጵያ ባሕላዊ መድኃኒቶች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.03.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ባሕላዊ መድኃኒቶች ወደ ፋብሪካ ምርት ሊሸጋገሩ ነው

ሀገሪቱ ለዘመናት ስትጠቀምባቸው የቆዩ 8 የባሕላዊ መድኃኒቶች በሳይንሳዊ መንገድ ተፈትሸው ለንግድ ምርት ዝግጁ መሆናቸውን የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ስምንቱ መድኃኒቶች ለባክቴሪያ፣ ለፈንገስ እና ለሌሎች የተለመዱ የጤና እክሎች መፍትሔ የሚሰጡ ሲሆን በቤተ ሙከራና በክሊኒካዊ ፍተሻዎች ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው መረጋገጡን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

መድኃኒቶቹ የምርምር ምዕራፋቸውን አጠናቅቀው ወደ ፋብሪካ ምርት የሚሸጋገሩበት ዝግጅት መገባደዱም ተጠቁሟል።


"አሁን ካለንበት የምርምር ምዕራፍ ወደ ኢንዱስትሪ እየተሻገርን ነው። ቀጣዩ ወሳኝ እርምጃ አምራቾችን በማሳተፍ ምርቱን በከፍተኛ መጠን ማምረትና የገበያ ፈቃድ አግኝቶ ሕዝቡ ጋር እንዲደርስ ማድረግ ነው" ሲሉ በኢንስቲትዩቱ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ረ/ፕ መሳይ ወልደማርያም ተናግረዋል፡፡


ይህ እርምጃ የውጭ መድኃኒት ጥገኝነትን ከመቀነሱ ባለፈ፤ የሀገሪቱን የባሕላዊ ሕክምና ዕውቀት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚቀይር እንደሚሆን ታምኖበታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0