አልጄሪያ እና ኒጀር አጋርነታቸውን ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር ዝግጁነታቸውን ገለፁ

ሰብስክራይብ

አልጄሪያ እና ኒጀር አጋርነታቸውን ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር ዝግጁነታቸውን ገለፁ

የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፊ ግሪብ ከኒጀር አቻቸው ዓሊ ማሃማን ላሚን ዜን ጋር የሁለቱን ሀገራት ከፍተኛ የጋራ ኮሚሽን ሁለተኛ ጉባኤ ሰኞ ዕለት በኒያሜ በሊቀመንበርነት መርተዋል። ሀገራቱ በጉባኤው ትብብራቸውን ይበልጥ ለማስፋት መስማማታቸውን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ቅድሚያ ለመስጠት የተስማሙባቸው ጉዳዮች፦

◻ እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶችን ማጠናከር፣

◻ ዋና ዋና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማፋጠን፣

◻ የኢኮኖሚ አጋርነትን ማሳደግ።

▪በአልጄሪያ በኩል በሰሜን አፍሪካ (ማግሬብ) እና በምዕራብ አፍሪካ መካከል ለሚፈጠሩ የወደፊት የኢኮኖሚ ኮሪደሮች ምሶሶ የሆኑት የትራንስ-ሳሃራ አውራ ጎዳና፣ የትራንስ-ሳሃራ የጋዝ ማስተላለፊያ እና የፋይበር ኦፕቲክ መሠረተ ልማቶችን ማፋጠን አስፈላጊ እንደሆነ አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

▪የኒጀር ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው በመሠረተ ልማት፣ በኢነርጂ፣ በነዳጅ እና ጋዝ፣ በማዕድን፣ በትራንስፖርት፣ በጤና እንዲሁም በግብርና ዘርፎች ያላቸውን የጋራ አቅም አንስተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0