"በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ የየውጤት ማሳጣት ሴራ እየተፈጸመ ነው" - ጋዜጠኛ ቦጋለ አበበ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.03.2026
ሰብስክራይብ
"በኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ የውጤት ማሳጣት ሴራ እየተፈጸመ ነው" - ጋዜጠኛ ቦጋለ አበበ

የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ቦጋለ አበበ ይህን ያለው፤ ፖላንድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጽጌ ዱጉማና ሦስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን በ21ኛው የቶሩን የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንዳይሳተፉ ቪዛ መከልከሏን አስመልክቶ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስተያየቱን በሰጠበት ወቅት ነው፡፡

‍‍ አትሌቶቹ በቪዛ ምክንያት በውድድሩ አለመሳተፋቸው፤ የሀገሪቱን ስፖርታዊ የበላይነት ለመቀነስ የታቀደ "የውጤት ማሳጣት ተግባር" እንደሆነ ገልጿል።


"የሆነ የውጤት ማሳጣት ሴራ እንደሚፈጸም ነው እኔ አሁን እየገባኝ ያለው... እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የታዳጊ ሀገራት አትሌቶች በቪዛ ሂደት፣ በተለያዩ ፖለቲካዊ አንደምታ ባላቸው ጉዳዮች ምክንያት ቪዛ እያጡ ዕድላቸውን መጠቀም እየቻሉ አይደለም" ሲል ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው ክልከላው ለኢትዮጵያም ሆነ ለአትሌቶች ትልቅ ጉዳት እንደሆነ ሲብራራ፤ "ቪዛ ባለማግኘታቸው ምክንያት የቀሩ አትሌቶች ተጎጂዎች ናቸው። ራሳቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያሳዩበት፤ ነገ በኦሊምፒክና የተለያዩ የግል ውድድሮች ላይ የሚጋበዙበትን ዕድል ነው የሚያሳጣቸው። እንደ ሀገር ካየነውም የምናጣቸው የሜዳሊያዎች ቁጥር በጣም ብዙ ናቸው” ብሏል፡፡


"ኢትዮጵያ ትታወቅበት በነበረው የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና ከ25 ዓመት በኋላ ምንም ዓይነት ሜዳሊያ ሳታገኝ እንድትመለስ ነው ያደረጋት። ይሄ እንደ ውጤት ትልቅ ቀውስ ነው፤ የሩብ ክፍለ ዘመን ታሪክ ተበላሸ ማለት ነው።"


ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0