ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ለባለሀብቶች ካስተላለፈችው 2.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው 45 በመቶ ብቻ ነው ተባለ
15:48 24.03.2026 (የተሻሻለ: 15:54 24.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ለባለሀብቶች ካስተላለፈችው 2.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው 45 በመቶ ብቻ ነው ተባለ
የግብርና ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር ባካሄደው የምክክር መድረክ፤ በሀገሪቱ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የውጭ ምርት ጥገኝነትን ለመቀነስ የግል ባለሀብቱ ሚና ወሳኝ ቢሆንም የዘርፉ አፈጻጸም ግን አሁንም ፈታኝ ሆኖ መቀጠሉ ተገልጿል።
ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ ለ8,742 ባለሀብቶች ከተላለፈው 2.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ በንቁ ልማት ላይ የሚገኘው ከግማሽ በታች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ይህን ለማሻሻል ተግባራዊ የተደረገው አዲሱ የግብርና እና ገጠር ልማት ፖሊሲ ለኢንቨስትመንት ልዩ ትኩረት መስጠቱን ጠቅሰው ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።
መንግሥት የግብርናውን ዘርፍ ውጤታማ ለማድረግና የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ለማጠናከር የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የድጋፍ ሥራዎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ጠቅሶ የዘገበው የሀገር ውስጥ ሚዲያ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X