የቤኒን ገዥ ፓርቲ ዕጩ ጂሃዲስቶችን ለመዋጋት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ፖሊስ ለማሰማራት ቃል ገቡ
14:46 24.03.2026 (የተሻሻለ: 14:57 24.03.2026)

ሰብስክራይብ
የቤኒን ገዥ ፓርቲ ዕጩ ጂሃዲስቶችን ለመዋጋት በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል ፖሊስ ለማሰማራት ቃል ገቡ
እ.ኤ.አ ሚያዝያ 12 በሚካሄደው ምርጫ አሸናፊ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁት ሮሙዋልድ ዋዳግኒ፤ የምርጫ ቅስቀሳቸውን ባቀረቡበት ወቅት ይህንን ዕቅድ ይፋ እንዳደረጉ አንድ የምዕራባውያን የዜና ወኪል ዘግቧል።
የዋዳግኒ የቅስቀሳ ዘመቻ ንግግር በኒጀር እና በናይጄሪያ የድንበር አካባቢዎች በሳኅል ቀጣና በሚንቀሳቀሱ አማፂያን የሚሰነዘሩ ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ የመጣ ነው።
“ዓላማው ወጣቶች በራሳቸው አካባቢ እንዲሠለጥኑ፣ እንዲታጠቁ እና ቤታቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ወንድም እህቶቻቸውን እንዲሁም አካባቢያቸውን የመከላከል ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የቤኒን ሰሜናዊ ግዛቶች በብሔራዊ ሪፐብሊካን ፖሊስ እና በሠራዊቱ ጥበቃ እየተደረገላቸው ይገኛል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X