አፍሪካን ያላካተተ ዓለም አቀፍ መድረክ ከዚህ ወዲህ ተቀባይነት አይኖረውም - የሕግ መምህር
11:35 24.03.2026 (የተሻሻለ: 12:09 24.03.2026)

ሰብስክራይብ
አፍሪካን ያላካተተ ዓለም አቀፍ መድረክ ከዚህ ወዲህ ተቀባይነት አይኖረውም - የሕግ መምህር
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አሁን ያለውን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ እንዲያንጸባርቅ አስቸኳይ መዋቅራዊ ለውጥ ያስፈልገዋል ሲሉ የአርሲ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ጃራ ሳሙኤል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
“ተመድ የተመሠረተው ከ70-80 ዓመታት በፊት በነበረ እውነታ ላይ በመሆኑ፤ አሁን ያለውን የዓለም ኃይል ሚዛን አይወክልም። አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት ይገባል” ብለዋል።
መምህሩ አክለውም የጸጥታው ምክር ቤት በአፍሪካ ጉዳይ ሌሎች የሚወስኑበት መድረክ መሆኑ ማብቃት እንዳለበት አስረድተዋል።
“አሁን በተለይ ታላላቅ ሀገራት አፍሪካን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት በፊት እንደነበረው አይደለም። አሁን ላይ አፍሪካ ቁልፍ ሚና እንደምትጫወት ሁሉም እያወቀው የመጣበት ጊዜ ነው።...አፍሪካን ቸል ብሎ፣ አፍሪካን ያላካተተ ፎረም ከአሁን በኋላ ተቀባይነቱ ጥያቄ ውስጥ ይገባል።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X