“በኃይል አምራቾች መካከል የሚደረግ ትብብር ከባድ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ሊከላከል ይችላል” - የአንጎላ የኢነርጂ ዲፕሎማሲ ባለሙያ
10:50 24.03.2026 (የተሻሻለ: 11:15 24.03.2026)

ሰብስክራይብ
“በኃይል አምራቾች መካከል የሚደረግ ትብብር ከባድ ዓለም አቀፋዊ ቀውስ ሊከላከል ይችላል” - የአንጎላ የኢነርጂ ዲፕሎማሲ ባለሙያ
በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት፣ የዋጋ መዋዠቅ እና የአቅርቦት ስጋቶች ሳቢያ የኃይል (ኢነርጂ) ገበያዎች እያደገ ለመጣ ጫና ተጋልጠዋል።
የዘርፉ ባለሙያ ሴባስቲያኦ ማቲውስ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፤ ሀገራት በአምራች ክልሎች መካከል በሚደረጉ አዳዲስ አጋርነቶች አማካኝነት መረጋጋትን ለማጽናት የሚያስችሉ መንገዶችን እየፈለጉ ነው።
“እንደ ናይጄሪያ ያሉ ሀገራት ያልተነካ የኃይል አቅም አላቸው፤ ይህም ከባሕረ ሰላጤው አምራቾች የልምድ ተሞክሮ እና የኢንቨስትመንት አቅም ጋር ከተጣመረ፤ የበለጠ የተረጋጋ እና አስቀድሞ መተንበይ የሚቻል ዓለም አቀፍ ገበያ ሊፈጥር ይችላል።”
የናይጄሪያ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ከሌሎች ክልሎች የሚመጣው አቅርቦት በሚስተጓጎልበት ወቅት ክፍተቶችን ለመሙላት ይረዳል፡፡ በሌላ በኩል በነዳጅ ማጣሪያ ላይ የሚደረጉ ተከታታይ ኢንቨስትመንቶችም በገቢ ዕቃዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ቀስ በቀስ እየቀነሱት እንደሚገኙ ባለሙያው ጠቁመዋል።
"ናይጄሪያ የኤክስፖርት ገቢዋን በማሳደግ ተዓማኒ አቅራቢነቷን ማጠናከር ትችላለች። ይህ ፈጣን የፋይናንስ ጥቅም ከማስገኘት ባለፈ፤ በኃይል መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶችን ለማጠናከር እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለማሳደግ ዕድል ይሰጣታል።"
ማቲውስ አክለውም በመሠረተ ልማት እና በደህንነት ላይ የሚከናወኑ የጋራ ፕሮጀክቶች የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ሊያጠናክሩ እና ወሳኝ የሆኑ ተቋማትን ከአደጋ ሊጠብቁ ይችላሉ ብለዋል።
በተጨማሪም ትብብሩ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ እና ታዳሽ ኃይሎች የሚደረገውን ማስፋፊያ ሊደግፍ እንደሚችል ጠቁመው፤ ይህም ሁለቱ ክልሎች የወጪ ንግድ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ እና ዓለም አቀፋዊ የኃይል ፅናትን እንዲያሳድጉ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X