አፍሪካ በማዳበሪያ ዋጋ መናር ታይቶ የማይታወቅ የምግብ ዋስትና ስጋት ገጥሟታል - የዋፋ ማዳበሪያ ቦርድ

አፍሪካ
አፍሪካ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.03.2026
ሰብስክራይብ
አፍሪካ በማዳበሪያ ዋጋ መናር ታይቶ የማይታወቅ የምግብ ዋስትና ስጋት ገጥሟታል - የዋፋ ማዳበሪያ ቦርድ

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት በማዳበሪያ ገበያ ላይ እውነተኛ መስተጓጎል እየፈጠረ ነው ሲሉ የዋፋ የማዳበሪያ ቦርድ አባል ማሊክ ኒያንግ ተናግረዋል።


"ስጋቱ ቀጥተኛ እና አሳሳቢ እንዲሁም ሦስትዮሽ መዘዝ አለው" ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ አስረድተዋል።


የመጀመሪያው፤ ከሎጂስቲክ መስመሮች መዘጋት ጋር የተያያዘ የአቅርቦት መስተጓጎል ነው። በግምት ከ16 እስከ 17 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያልፈው በሆርሙዝ ወሽመጥ ነው።

ሁለተኛው፤ "የናይትሮጂን ማዳበሪያ ምርት 80% ወጪ" የሆነው የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ በመጨመሩ የሚፈጠረው ከፍተኛ የዋጋ መናር ነው። የመጨረሻው የአፍሪካ ግብርና መዋቅራዊ ተጋላጭነቶች እየተባባሱ መምጣታቸው ነው።

ከእስያ በሄክታር ከ130 እስከ 140 ኪ.ግ የማዳበሪያ አጠቃቀም ጋር ሲነጻጸር ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በሄክታር ከ15 እስከ 17 ኪ.ግ ብቻ ይጠቀማሉ።


"በጣም አነስተኛ የዋጋ ጭማሪ እንኳን አጠቃቀም ላይ በሚስከትለው ቅነሳ [...] ምርታማነት ላይ ወዲያውኑ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል" ሲሉ ኒያንግ አስጠንቅቀዋል።


በቀውሱ ሳቢያ የአኅጉሪቱ የምግብ ዋስትና ከመቼውም ጊዜ በላይ አደጋ ላይ እንደወደቀ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0