ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት የጤና ዘርፍ በጀቷን በሦስት እጥፍ ማሳደጓ ተገለፀ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት የጤና ዘርፍ በጀቷን በሦስት እጥፍ ማሳደጓ ተገለፀ

ይህ እርምጃ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) እ.ኤ.አ በ2025 በዓለም አቀፍ ደረጃ ሥራውን ማቆሙን ተከትሎ የተፈጠረውን የገንዘብ ክፍተት ለመሙላት መወሰዱን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ፤ የውጭ ዕርዳታ መቀነስን የሀገሪቱን አቅም ለማሳየት እንደ ጥሩ ዕድል በመጠቀም፤ መንግሥት ገንዘብ በማሰባሰብ ክፍተቶችን እየሞላ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ከ11 አጋሮች ጋር በመሆን በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት 284 ሚሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ ማቀዱንና የገንዘብ ሚኒስቴርም ለዚሁ ፕሮግራም ተጨማሪ 140 ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ዶ/ር ደረጄ ገልፀዋል።

ከ85 በመቶ በላይ የሚሆኑ የቤተሰብ ምጣኔ፣ የእናቶችና የሕፃናት ጤና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በሀገር ውስጥ ግዢ በመፈጸም በቀጥታ ለተረጂዎች ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱንም ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0