"ይህ ትብብር ሳይሆን ቅኝ አገዛዝ ነው" - የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአውሮፓ ኅብረት የወረርሽኝ ስምምነት ላይ ተቃውሞ አቀረቡ
19:39 23.03.2026 (የተሻሻለ: 19:44 23.03.2026)
ሰብስክራይብ
"ይህ ትብብር ሳይሆን ቅኝ አገዛዝ ነው" - የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአውሮፓ ኅብረት የወረርሽኝ ስምምነት ላይ ተቃውሞ አቀረቡ
ኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች፤ የአውሮፓ ኅብረት ሕይወት አድን የሆኑ የወረርሽኝ መከላከያ መሣሪያዎች ፍትሐዊ ተደራሽነት ላይ እንቅፋት እየሆነ ነው ሲሉ ተችተዋል።
ጉዳዩ በግንቦት ወር 2025 የጸደቀው የበሽታ አምጪ ተዋሲያን መረጃ ተደራሽነት እና ማጋራት ስምምነትን የተመለከተ ነው። የአውሮፓ ኅብረት የአፍሪካ ሀገራት የበሽታ አምጪ ተዋሲያን መረጃን እንዲያጋሩ የሚያስገድድ፤ ነገር ግን ከመረጃው የሚሠሩ ክትባቶች እና ሕክምናዎች ለሀገራቱ ስለሚደርሱበት ሁኔታ ምንም ዓይነት ዋስትና የማይሰጥ አሠራር እንዲዘረጋ ግፊት እያደረገ ይገኛል።
የማኅበራቱ ጥምረት ባልደረባ አበበ ከበደ፤ "ከደቡባዊው የዓለም ክፍል መረጃን ወስዶ በሰሜናዊው የዓለም ክፍል ትርፋማ ምርቶችን በማምረት እነዚሁኑ ምርቶች በማይቀመስ ዋጋ መልሶ የሚሸጥ አሠራርን ፈጽሞ አንቀበልም" ብለዋል።
የተቀናጀ የጤና እና ልማት አገልግሎት ድርጅት ባልደረባ አክሊሉ ነጋ በበኩላቸው "የጤና ሉዓላዊነት ለአፍሪካ ሊደረስበት የማይችል ህልም መሆን የለበትም" ሲሉ አክለዋል።
የግንቦት 2026 የመጨረሻ የጊዜ ገደብ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት፤ ድርጅቶቹ አስገዳጅ የሆኑ የፍትሐዊነት ደንቦች ካልጸደቁ ግማሹ የዓለም ክፍል ለሚቀጥለው ወረርሽኝ መከላከያ እንደማይኖረው አስጠንቅቀዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X