ደቡብ አፍሪካ በአውሮፓ ለዘመናት የቆዩ 63 የቀደምት ትውልድ አጽሞችን ዳግም ቀበረች

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ በአውሮፓ ለዘመናት የቆዩ 63 የቀደምት ትውልድ አጽሞችን ዳግም ቀበረች

ከአውሮፓ አጽሞችን የማስመለስ ጥረት አካል የሆነውን ሥነ-ሥርዓት የመሩት ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ፤ የኮይ እና የሳን ተወላጆችን አጽም ሰኞ ዕለት ዳግም በደቡብ አፍሪካ ምድር አሳርፈዋል።

መንግሥታቸው ባወጣው መግለጫ "እነዚህ ለአዳዲስ ሙዚየሞች እና ዩኒቨርሲቲዎች ሊሸጡ ወይም በስጦታ ሊቀርቡ ይችሉ የነበሩት አጽሞች፤ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ እና በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ በሕገ-ወጥ መንገድ ከተወሰዱ በሺዎች የሚቆጠሩ የቀደምት ሕዝቦች አጽሞች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው" ብሏል።

መግለጫው አክሎም የሳን እና የኮይ ሕዝቦች ለዘመናት የቆየ መጠነ-ሰፊ በደል ሰለባ እንደነበሩ አጽንኦት ሰጥቷል፦

የቅኝ ግዛት ወረራ፣

ከመሬታቸው መፈናቀል፣

የባሕል መጥፋት እና መወገድ፣

በዘር ላይ የተመሠረተ ሳይንሳዊ ምርምር ሰለባ መሆን፣

የቀደምት ትውልድ አጽሞች ብዝበዛ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0