ኮትዲቯር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞዋ እንዲፋጠን የሚረዳ በጀት አገኘች
ሀገሪቱ የዲጂታል ክፍተትን ለማጥበብ እየሰራች ትገኛለች። እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ በ2025 መገባደጃ የሀገሪቱ የኢንተርኔት ተደራሽነት 40.7 በመቶ ነበር።
ኮትዲቯር ለዲጂታል ተደራሽነት ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ከዓለም ባንክ 152 ሚሊዮን ዶላር እንዳገኘች ይፋዊ መረጃዎች አሳይተዋል።
አቢጃን በተለይም በገጠር አካባቢዎች ያለውን የኢንተርኔት ተደራሽነት ችግር ለመፍታት ወደ ሳተላይት ቴክኖሎጂዎች ፊቷን በማዞር ከመስከረም 2025 ጀምሮ ፈቃድ ያገኘውን የስታርሊንክ አገልግሎት መጠቀም ጀምራለች።
የኮትዲቯር የዲጂታል ሽግግር እና ዲጂታላይዜሽን ሚኒስትር “በሳተላይት ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት በተሻለ ፍጥነት መጓዝ እንችላለን” ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም የኮትዲቯር መንግሥት ትኩረቱን በግንኙነት፣ በዲጂታል የሕዝብ አገልግሎቶች፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሳይበር ደህንነት ላይ በማደረግ ሀገሪቱን የምዕራብ አፍሪካ የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ እየሠራ ነው።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X