ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አነስተኛ አምራቾችን ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የሚቀይር አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.03.2026
ሰብስክራይብ
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አነስተኛ አምራቾችን ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የሚቀይር አዲስ አሠራር ይፋ አደረገ

የክልሉ የማዕድን ልማት ቢሮ አነስተኛ ወርቅ አምራቾችን በ5 ሄክታር መሬት ላይ በማደራጀት እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንዳደረገ የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።

አደረጃጀቱን በተመለከተ የተጠቀሱ አንኳር ነጥቦች፦

🟠 የአካባቢው ነዋሪዎች የቆየ ልምድና እውቀታቸውን ከሕጋዊ አሠራር ጋር በማቀናጀት ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ዕድል ፈጥሯል፣
🟠 አምራቾቹን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተሻለ የኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሸጋገር በትኩረት እየተሠራበት ነው፣
🟠 ባለሀብቶች ከአነስተኛ አምራቾች ጋር በጋራ እንዲሠሩ ወይም ከ5 እስከ 50 ሄክታር መሬት በመስጠት በኩባንያ ደረጃ እንዲንቀሳቀሱ ሂደቶች እየተመቻቹ ይገኛል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ናስር መሐመድ ይህ ተነሳሽነት “የክልሉን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠንና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ነው” ብለዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉም ተገልጿል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0