የኢራን ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የቅንጦት መኪኖችን መሄጃ አሳጥቶ በላሙ ወደብ አስቀርቷል

ሰብስክራይብ

የኢራን ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ የቅንጦት መኪኖችን መሄጃ አሳጥቶ በላሙ ወደብ አስቀርቷል

ፖርሽ እና ቮልስዋገንን ጨምሮ ከ4 ሺህ በላይ የቅንጦት መኪኖች በሆርሙዝ ወሽመጥ በተፈጠረው መስተጓጎል ምክንያት ከመዳረሻቸው ዱባይ ወደ ኬንያ እንዲዛወሩ ተደርጓል።

መኪኖቹ በላሙ ወደብ መራገፋቸውን እና ሁኔታዎች እስኪረጋጉ ድረስ እዛው እንደሚቆዩ የወደቡ ባለሥልጣናት አረጋግጠዋል። በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ 5 ሺህ ተሽከርካሪዎች ወደ ወደቡ ይደረሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኬንያ ባለሥልጣናት ወደቡ እየጨመረ የመጣውን የተሽከርካሪ ብዛት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ቢገልጹም፤ የቅንጦት መኪኖቹን እጣ ፈንታ በተመለከት ግን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0