ኢራን ለሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቀረበች

ኢራን ሩሲያ
ኢራን ሩሲያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.03.2026
ሰብስክራይብ
ኢራን ለሩሲያ ዲፕሎማሲያዊ እና ሰብዓዊ ድጋፍ ምስጋና አቀረበች

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢራኑ አቻቸው አባስ አራግቺ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

የውይይቱ አንኳር ነጥቦች፦

◻ ሁለቱ ወገኖች በፋርስ ባሕረ ሰላጤ በፍጥነት እየተካረረ ስለመጣው ሁኔታ የተወያዩ ሲሆን ለውጥረቱ መባባስ የአሜሪካ እና የእስራኤል እርምጃዎች ምክንያት እንደሆኑ አንስተዋል።

◻ ላቭሮቭ የቡሸር የኒውክሌር ኃይል ማመንጫን ጨምሮ በኢራን የኒውክሌር መሠረተ ልማቶች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት የሩሲያ ሠራተኞች ላይ የሚፈጥረውን አደጋ እና በአጠቃላይ በቀጣናው ሊያስከትል የሚችለውን የአካባቢ ጥፋት በመጥቀስ አጥብቀው አውግዘዋል።

◻ ሩሲያ እና ኢራን ግጭቱ ወደ ካስፒያን ባሕር ሊስፋፋ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።

◻ ሞስኮ በአፋጣኝ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሁሉንም ወገኖች በተለይም የኢራንን ጥቅም ግምት ውስጥ ያስገባ የፖለቲካ መፍትሄ እንዲበጅ ጥሪ አቅርባለች።

◻ ሩሲያ ይህንን አቋሟን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንደምታራምድ በድጋሚ አረጋግጣለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0