ኒጄራውያን በሞሐመድ ባዙም ላይ የወጣውን የአውሮፓ ኅብረት ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ ወጡ

ሰብስክራይብ
ኒጄራውያን በሞሐመድ ባዙም ላይ የወጣውን የአውሮፓ ኅብረት ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ ወጡ

ባሳለፍነው ሳምንት የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የቀድሞው ፕሬዚዳንት "በአስቸኳይ እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ" እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡ ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የሳኅል ሀገራት ጥምረትን ቁጣ ቀስቅሶ ነበር።

የኒጀር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ይህንን ጥያቄ ከሰልፈኞች ጋር በመሆን አውግዘዋል፦

የአውሮፓን ኅብረት፣ ኢምፔሪያሊዝምን እና በኒጀር ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም መፈክሮችን አሰምተዋል፣
ለውይይት፣ ለሰላም እና ለሰብዓዊ መብቶች ቁርጠኝነታቸውን ዳግም አረጋግጠዋል፣
ሀገራዊ ጉዳዮች በኒጀር ሕዝብ እና በተቋሞቻቸው ብቻ መፈታት እንዳለባቸው ኣሳስበዋል።

በሰልፉ ማጠቃለያ በኒጀር ላይ እየተደረገ ያለው ውጫዊ ጫና አሳሳቢ መሆኑን የሚገልጽ መግለጫ ተነቧል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሰኔ 2024 ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ በኒያሜ መንግሥት በሀገር ደህንነት ላይ በማሴር፣ በሀገር ክህደት እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ በመርዳት ተከሰዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0