አልጄሪያ የዚንክ እና ሊድ ማዕድን ቁፋሮ ሥራ ጀመረች
16:59 22.03.2026 (የተሻሻለ: 17:04 22.03.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አልጄሪያ የዚንክ እና ሊድ ማዕድን ቁፋሮ ሥራ ጀመረች
በአልጄሪያ ሰሜን ምስራቅ ቤጃያ በተባለ አካባቢ የሚገኘውና በዓለማችን ካሉ እጅግ የበለፀጉ የማዕድን ክምችቶች አንዱ የሆነው ይህ የማዕድን ስፍራ፤ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪን ለማጠናከር እና አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
የፕሮጀክቱ ቁልፍ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦
የታቀደ ዓመታዊ ምርት፦ 170 ሺህ ቶን ዚንክ እና 30 ሺህ ቶን ሊድ፣
የተገመተ የማዕድን ክምችት፦ 34 ሚሊዮን ቶን ያልተጣራ ማዕድን፣
የሚጠበቅ ዓመታዊ ገቢ፦ ወደ 215 ሚሊዮን ዶላር ገደማ።
ይህ ፕሮጀክት ለእነዚህ ማዕድናት ያለውን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ከማሟላቱም በላይ ምርቱን ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ መንገድ ይከፍታል ተብሏል።
ቪዲዮው የአልጄሪያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲፊ ግሪብ ረቡዕ ዕለት ፕሮጀክቱን ሲያስመርቁ ያሳያል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X