የኢትዮጵያ ደኖች የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ደን ልማት
የኢትዮጵያ ደን ልማት  - Sputnik አፍሪካ, 1920, 22.03.2026
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ደኖች የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ነው ተባለ


“የሀገሪቱ ደኖች 2.7 ቢሊዮን ቶን የካርበን ክምችት በመያዝ ዓለምን ከብክለት እየታደጉ ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ደን ልማት ዋና ዳይሬክተር ከበደ ይማም ለሀገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡


ይህ የካርበን መጠን ባይኖር ወይም ደኖቹ ቢወድሙ፤ ወደ 10 ቢሊዮን ቶን የሚጠጋ የካርበን ዳይኦክሳይድ ጋዝ በቀጥታ ወደ አየር ሊለቀቅ እንደሚችልና የአየር ንብረት ብክለትን በከፍተኛው ያባብስ እንደነበር ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ የደን ልማት ሀገራዊ ፋይዳንም አንስተዋል፦

ለሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ከፍተኛ የሚባል ድርሻ አለው፣
ከ28-47% የሚሆነው የኅብረተሰብ ክፍል ከደን ሀብት ቀጥተኛ ገቢ ያገኛል፡፡

ኢትዮጵያ የካርበን ክምችቷን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ገቢ ለማግኘት እየሠራች እንደሆነም ተጠቁሟል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
አዳዲስ ዜናዎች
0